መሳፍንት 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፤ ሄዶም እስራኤልን መታ፤ ዘንባባ ያለባትንም ከተማ ያዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎች ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎችበ ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔግሎንም ዐሞናውያንንና ዐማሌቃውያንን አስተባብሮ እስራኤልን ወጋ፤ የተምር ዛፍ የሞላባትንም የኢያሪኮን ከተማ በቊጥጥራቸው ሥር አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፥ ሄዶም እስራኤልን መታ፥ ዘንባባም ያለባትን ከተማ ያዙአት። |
የቄናዊው የሙሴ አማት የዮባብ ልጆችም ከዘንባባ ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በአዜብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፥ “ግብፃውያን፥ አሞሬዎናውያንም፥ የአሞንና የሞአብም ልጆች፥ ፍልስጥኤማውያንም፥
ሲዶናውያንም፥ ምድያማውያንም፥ አማሌቃውያንም አላስጨነቋችሁምን? ወደ እኔም ጮኻችሁ፤ እኔም ከእጃቸው አዳንኋችሁ።
የአሞንም ልጆች ከይሁዳ፥ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ! በሕዝብ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፤ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።
የእስራኤልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያንና አማሌቃውያን ይዘምቱባቸው ነበር፥ በምሥራቅም የሚኖሩ ልጆች አብረው ይዘምቱባቸው ነበር፤