Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዔግሎንም ዐሞናውያንንና ዐማሌቃውያንን አስተባብሮ እስራኤልን ወጋ፤ የተምር ዛፍ የሞላባትንም የኢያሪኮን ከተማ በቊጥጥራቸው ሥር አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎች ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎችበ ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የአ​ሞ​ንን ልጆ​ችና አማ​ሌ​ቅን ወደ እርሱ ሰበ​ሰበ፤ ሄዶም እስ​ራ​ኤ​ልን መታ፤ ዘን​ባባ ያለ​ባ​ት​ንም ከተማ ያዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፥ ሄዶም እስራኤልን መታ፥ ዘንባባም ያለባትን ከተማ ያዙአት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 3:13
9 Referencias Cruzadas  

ኔጌብንና ሜዳውን፥ የኢያሪኮን ሸለቆ የዘንባባዎች ከተማ የምትባለውን ኢያሪኮን፥ እስከ ጾዓር ድረስ አሳየው።


የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ።


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ግብጻውያን፥ አሞራውያን፥ ዐሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ሲዶናውያን፥ ዐማሌቃውያንና ማዖናውያን ከዚህ በፊት ጨቊነው በገዙአችሁ ጊዜ ወደ እኔ ጮኻችሁ ነበር፤ ታዲያ እኔስ ከእነርሱ ጭቈና በመታደግ አድኛችሁ አልነበረምን?


ዐሞናውያን የይሁዳን፥ የብንያምንና የኤፍሬምን ነገዶች ለመውጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨነቁ።


የእስራኤል ሕዝብ ለዐሥራ ስምንት ዓመት ለሞአብ ንጉሥ ለዔግሎን ተገዢዎች ሆኑ።


ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።


እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ምድያማውያን፥ ከዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች እየመጡ አደጋ ይጥሉባቸው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos