መሳፍንት 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነሥተው እንዲህ አሉ፥ “ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ሀገሩ አይሄድም፤ ወደ ቤቱም አይመለስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው በመነሣት እንዲህ አሉ፤ “ከእኛ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፤ ማንኛችንም ወደ ቤታችን አንመለስም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው በመነሣት እንዲህ አሉ፤ “ከእኛ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፤ ማንኛችንም ወደ ቤታችን አንመለስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም ሁሉ በአንድነት ቆመው እንዲህ አሉ፤ “ከእኛ መካከል በድንኳንም ሆነ በቤት ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው ወደ ቤቱ አይመለስም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነሥተው አሉ፦ ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ድንኳኑ አይሄድም፥ ወደ ቤቱም አይመለስም። |
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ስላልወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበርና፥ “ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግዚአብሔር ያልወጣ ማን ነው?” አሉ።