መሳፍንት 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብላቴናዪቱም አባት አማቱ ወደ ቤቱ አገባው፤ በቤቱም ሦስት ቀን ተቀመጠ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ በዚያም አደሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅቱ አባትም እዚያው እንዲቈይ አጥብቆ ለመነው፤ ስለዚህ እየበላ እየጠጣ ሦስት ቀን ዐብሮት ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልጂቱ አባትም እዚያው እንዲቈይ አጥብቆ ለመነው፤ ስለዚህ እየበላ እየጠጣ ሦስት ቀን አብሮት ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያ እንዲቈይ አደረገው፤ እርሱም ሦስት ቀን በዚያ ቈየ፤ እዚያም እየበሉና እየጠጡ ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብላቴናይቱም አባት አማቱ የግድ አለ፥ በቤቱም ሦስት ቀን ተቀመጠ፥ በሉም፥ ጠጡም፥ በዚያም አደሩ። |
አብርሃምም ለቁባቶቹ ልጆች ሀብትን ሰጣቸው፤ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ምሥራቅ ሀገር ሰደዳቸው።
ባልዋም ተነሣ፤ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር አንድ ብላቴና፥ ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብላቴናዪቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀበለው።
በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፤ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት አማቹን፥ “ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው።