መሳፍንት 19:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕቅብቱም ተጣላችው፤ ትታውም ወደ አባቷ ቤት ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔም ሄደች፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቁባቱ ግን አመነዘረች፤ ትታውም በይሁዳ ምድር ወደሚገኘው ወደ አባቷ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ሄደች፤ እዚያም አራት ወር ከቈየች በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱ ግን በታማኝነት አልጸናችም፤ ትታውም በይሁዳ ምድር ወደሚገኘው ወደ አባቷ ቤት ወደ ቤተልሔም ሄደች፤ እዚያም አራት ወር ከቈየች በኋላ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ልጅቱ ከእርሱ ጋር ተጣልታ በቤተልሔም ወደሚገኘው ወደ አባቷ ቤት ኮብልላ ሄደች፤ በዚያም አራት ወር ቈየች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቁባቱም አመነዘረችበት፥ ትታውም ወደ አባትዋ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄደች፥ በዚያም አራት ወር ተቀመጠች። |
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
በዚያም ዘመን ለእስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይሁዳ ቤተ ልሔምም ዕቅብት አገባ።
ባልዋም ተነሣ፤ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር አንድ ብላቴና፥ ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብላቴናዪቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀበለው።