በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
መሳፍንት 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናል፤ ተነሡ፤ በእነርሱ ላይ እንውጣ፤ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኞቹም እንዲህ አሏቸው፤ “ምድሪቱ እጅግ መልካም መሆኗን አይተናል፤ እንግዲህ ተነሡ! ሄደን እንዋጋቸው፤ ተነሡ እንጂ ዝም ትላላችሁን? ወደዚያው ሄዳችሁ ምድሪቱን ለመያዝ አታመንቱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልእክተኞቹም እንዲህ አሏቸው፤ “ምድሪቱ እጅግ መልካም መሆኗን አይተናል፤ እንግዲህ ተነሡ ሄደን እንዋጋቸው፤ ተነሡ እንጂ ዝም ትላላችሁን? ወደዚያው ሄዳችሁ ምድሪቱን ለመያዝ አታመንቱ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “እንግዲህ ኑ! በላዪሽ ላይ አደጋ እንጣል! ምድሪቱ በጣም ጥሩ መሆንዋን አይተናል፤ እዚህ ያለ ሥራ ቦዝናችሁ አትቀመጡ፤ ይልቅስ በፍጥነት ሄዳችሁ ያዙአት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናልና ተነሡ፥ በእነርሱ ላይ እንውጣ፥ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ። |
በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።”
የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን፥ “ሬማት ዘገለዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶርያ ንጉሥ እጅ ሳንወስዳት ዝም እንዳልን ታውቃላችሁን?” አላቸው።
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፥ “የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር እንዳትወርሱአት እስከ መቼ ድረስ ታቈዩአታላችሁ?
በሄዳችሁም ጊዜ ተዘልለው ወደ ተቀመጡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፤ ምድሪቱም ሰፊ ናት፤ እግዚአብሔርም በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጐድልባትን ስፍራ በእጃችሁ ሰጥቶአል” አሉ።
እነዚያም አምስቱ ሰዎች ወደ ወንድሞቻቸው ወደ ሶራሕና ወደ እስታሔል ተመለሱ፤ ወንድሞቻቸውንም፥ “ምን አስቀምጦአችኋል?” አሉአቸው።
እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እናንተ ባሪያዎች እንዳደረጋችኋቸው ዕብራውያን ባሪያዎች እንዳያደርጓችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።”