ከሳሪራ ሀገር የሆነ የኤፍሬማዊው የናባጥና ሳሩሃ የተባለች የመበለት ልጅ ኢዮርብዓም የሰሎሞን አገልጋይ ነበረ።
መሳፍንት 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መልካዎች ያዙ። ታዲያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፣ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬም ሰዎች እንዳያመልጡ ለማድረግ ገለዓዳውያን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ቦታዎች ሁሉ ዘግተው ያዙ፤ ለማምለጥ የሚሞክር ማንኛውም የኤፍሬም ሰው ለመሻገር ፈቃድ ቢጠይቅ ገለዓዳውያን “አንተ የኤፍሬም ሰው ነህን?” ብለው ይጠይቁት ነበር፤ “አይደለሁም!” ካለ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገለዓዳውያንም ኤፍሬም የሚያልፍበትን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙባቸው፥ የሸሸም የኤፍሬም ሰው፦ ልለፍ ባለ ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች፦ አንተ ኤፍሬማዊ ነህን? አሉት፥ እርሱም፦ አይደለሁም ቢል፥ |
ከሳሪራ ሀገር የሆነ የኤፍሬማዊው የናባጥና ሳሩሃ የተባለች የመበለት ልጅ ኢዮርብዓም የሰሎሞን አገልጋይ ነበረ።
የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በገለዓድ፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።
ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፤ ኤፍሬምም፥ “ገለዓዳውያን ሆይ! እናንተ በኤፍሬምና በምናሴ መካከል የተቀመጣችሁ ከኤፍሬም ሸሽታችሁ ነው” ስላሉ የገለዓድ ሰዎች ኤፍሬምን መቱ።
እነርሱም፥ “አሁን ሺቦሌት በሉ” አሉአቸው፤ እነርሱም አጥርተው መናገር አልቻሉምና፥ “ሲቦሌት” አሉ፤ ይዘውም በዮርዳኖስ መሸጋገርያ አረዱአቸው፤ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ።
እርሱም፥ “እግዚአብሔር አምላክ ጠላቶቻችንን ሞዓባውያንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ተከተሉኝ” አላቸው። ተከትለውትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓብም የሚያሻግረውን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እንዲያልፍ አልፈቀዱም።
ጌዴዎንም፥ “ምድያማውያንን ለመግጠም ውረዱ፥ እስከ ቤትባራም ድረስ ያለውን ውኃ፥ ዮርዳኖስንም፥ ያዙባቸው” ብሎ መልእክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ተራራማ ሀገር ሁሉ ላከ። የኤፍሬምም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው እስከ ቤትባራ ድረስ ውኃውን፥ ዮርዳኖስንም ቀድመው ያዙ።
በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የናሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤልዩ ልጅ ፥ የኢያርምያል ልጅ፥ ኤፍራታዊው ሕልቃና ነበረ።