ይሁዳም ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንን በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ገደለባቸው።
መሳፍንት 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም ሊዋጋቸው ወደ አሞን ልጆች ተሻገረ፤ እግዚአብሔርም በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዮፍታሔ አሞናውያንን ለመውጋት ወጣ፤ እግዚአብሔርም እርሱን በእጁ አሳልፎ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዮፍታሔ አሞናውያንን ለመውጋት ወጣ፤ ጌታ እነርሱን በእጁ አሳልፎ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ዮፍታሔ ዐሞናውያንን ለመውጋት ወንዙን ተሻግሮ ሄደ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድልን አጐናጸፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም ሊዋጋቸው ወደ አሞን ልጆች አለፈ፥ እግዚአብሔርም በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው። |
ይሁዳም ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንን በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ገደለባቸው።
ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚቀበለኝን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አደርገዋለሁ” ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ።
ከአሮዔርም እስከ ሚኒትና እስከ አቤልክራሚም ድረስ ሃያ ከተሞችን በታላቅ ሰልፍ አጠፋቸው። የአሞንም ልጆች በእስራኤል ልጆች ፊት ተዋረዱ።
እግዚአብሔርም መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር ነበረ፤ እግዚአብሔርም በሚዋጉአቸው ሰዎች ፊት ከመከራቸው የተነሣ ይቅር ብሏቸዋልና በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ አዳናቸው።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች።