ዕረፍትም መልካም መሆንዋን፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን በአየ ጊዜ ምድርን ያርሳት ዘንድ ትከሻውን ዝቅ አደረገ፤ በሥራም ገበሬ ሆነ።
መሳፍንት 1:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛብሎንም በቄድሮንና በአማን የሚኖሩትን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፤ ግብርም የሚገብሩላቸው ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከላቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከለቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዛብሎን ነገድ በቂትሮንና በናህላል ይኖሩ የነበሩትን ኗሪዎች አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህ ከነዓናውያን እዚያው ከእነርሱ ጋር ኗሪዎች ሆኑ፤ ሆኖም ለዛብሎናውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሎንም የቂድሮንንና የነህሎልን ሰዎች አላወጣቸውም፥ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፥ ግብርም የሚገብሩለት ሆኑ። |
ዕረፍትም መልካም መሆንዋን፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን በአየ ጊዜ ምድርን ያርሳት ዘንድ ትከሻውን ዝቅ አደረገ፤ በሥራም ገበሬ ሆነ።
ኤፍሬምም በጋዜር የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው በጋዜር ተቀመጡ፤ ገባሮችም ሆኑላቸው።
አሴርም የዓኮ ነዋሪዎችን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ገባሮች ሆኑላቸው፤ የዶር ነዋሪዎችንና የሲዶን ነዋሪዎችን፥ የደላፍንም ነዋሪዎች፥ የአክሶዚብንና የሄልባን፥ የአፌቅንና የረዓብንም ሰዎች አላጠፉአቸውም።