La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናንተም ከተደበቃችሁበት ትወጡና ከተማዪቱን ትይዛላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከተማዪቱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋልና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፤ ጌታም አምላካችሁ እርሷን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህን ጊዜ እናንተ ከተደበቃችሁበት ስፍራ ወጥታችሁ ከተማይቱን ያዙ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከተማይቱን ለእናንተ አሳልፎ ይሰጣችኋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:7
6 Referencias Cruzadas  

የሶ​ርያ ንጉሥ ሠራ​ዊት አለቃ ንዕ​ማ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ እጅ ለሶ​ርያ ደኅ​ን​ነ​ትን ስለ ሰጠ፥ በጌ​ታው ዘንድ ታላ​ቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰው​ዬ​ውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለም​ጻም ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋ​ይ​ንም ንጉሥ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ከተ​ማ​ው​ንም ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን።


በያ​ዛ​ች​ኋ​ትም ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አት፤ እንደ አል​ኋ​ችሁ አድ​ርጉ፤ እነሆ፥ አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”


ዳዊ​ትም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።