La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በጋ​ይና በቤ​ቴ​ልም ውስጥ እስ​ራ​ኤ​ልን ለማ​ሳ​ደድ ያል​ወጣ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከፍ​ተው ተዉ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ደ​ዱት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤልን ለማሳደድ ከጋይና ከቤቴል ያልወጣ ወንድ አልነበረም፤ ከተማዪቱንም ከፍተው ትተው እስራኤልን ማሳደድ ያዙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም፤ ከተማይቱንም ከፍተው ተዉ፥ እስራኤልንም አሳደዱት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዐይ ወይም በቤትኤል የሚገኝ ሰው ሁሉ ወጥቶ እስራኤላውያንን ሲያሳድድ ከተማይቱ ባዶዋን ክፍት ሆና ቀረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም፥ ከተማይቱንም ከፍተው ተዉ፥ እስራኤልንም አሳደዱት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:17
9 Referencias Cruzadas  

ጠቢ​ባ​ን​ንም በተ​ን​ኰ​ላ​ቸው ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ምክ​ርን የሚ​ጐ​ነ​ጉኑ ሰዎ​ችን አሳብ ያጠ​ፋል።


የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።


የሀ​ገ​ሪ​ቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲ​ርቁ አደ​ረ​ጓ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ጋይን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ጅህ ያለ​ውን ጦር በላ​ይዋ ዘርጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም የከ​በ​ቡ​አት ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ይነ​ሣሉ” አለው፤ ኢያ​ሱም በከ​ተ​ማዋ ላይ በእጁ ያለ​ውን ጦር ዘረጋ።


ኢያ​ሱም፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያ​ሱም ጽኑ​ዓን፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችና ኀያ​ላን የሆ​ኑ​ትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌ​ሊ​ትም ላካ​ቸው።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች በሕ​ዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጊዜ፥ በአ​ው​ራ​ዎቹ መን​ገ​ዶች፥ አን​ደ​ኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ወደ ገባ​ዖን ሜዳ በሚ​ወ​ስ​ዱት መን​ገ​ዶች ላይ ሕዝ​ቡን ይመቱ፥ ይገ​ድ​ሉም ጀመር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።