ኢያሱ 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደረሱባቸውም ጊዜ ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ከፊታቸው አፈገፈጉ፤ በምድረ በዳው መንገድም ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱና እስራኤል በሙሉ ድል የተመቱ መስለው በመታየት፣ ወደ ምድረ በዳው ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ የተሸነፉ በማስመሰል ወደ ኋላ በማፈግፈግ ወደ ምድረ በዳ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። |
የዮሴፍም ልጆች ድንበራቸው በኢያሪኮ አንጻር በምሥራቅ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ሎዛ ትባል ወደ ነበረችው ቤቴል ይደርሳል፤
በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ከኢያሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መውጫውም የቤቶን ምድብራይጣስ ነበረ።
የጋይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከተማዪቱም ሰዎች ወጡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ተቀበሉአቸው፤ እርሱ ግን ከከተማዪቱ በስተኋላ እንደ ተደበቁ አያውቅም ነበር።
የብንያም ልጆችም እንደ ተመቱ አዩ፤ የእስራኤል ልጆች ግን በገባዖን ላይ ባኖሩት ድብቅ ጦር ታምነዋልና ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው።
ከእስራኤልም ሰዎች ፊት ወደ ምድረ በዳ መንገድ ሸሹ፤ ሰልፉም ደረሰባቸው፤ ከየከተማውም የወጡት በመካከላቸው ገደሉአቸው።