La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከከተማዪቱ በስተሰሜን የነበሩትንም፣ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ የሸመቁትንም ወታደሮች ሁሉ ስፍራ ስፍራቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው፤ በዚያችም ሌሊት ኢያሱ ወደ ሸለቆው ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ዋናውን ሠራዊት ከከተማ በስተሰሜን በኩል፥ የኋላውን ደጀን በስተምዕራብ በኩል አሰለፉ፤ ኢያሱ ግን ሌሊቱን በሸለቆው አሳለፈ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:13
3 Referencias Cruzadas  

ኢያ​ሱም አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ወስዶ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል በጋይ ባሕር በኩል ይከ​ብቡ ዘንድ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው።


የጋ​ይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጡ፤ እር​ሱና ሕዝ​ቡም ሁሉ በተ​ወ​ሰ​ነው ጊዜ በዓ​ረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስ​ራ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እርሱ ግን ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ እንደ ተደ​በቁ አያ​ው​ቅም ነበር።


በያ​ዛ​ች​ኋ​ትም ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አት፤ እንደ አል​ኋ​ችሁ አድ​ርጉ፤ እነሆ፥ አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”