Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከከተማዪቱ በስተሰሜን የነበሩትንም፣ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ የሸመቁትንም ወታደሮች ሁሉ ስፍራ ስፍራቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው፤ በዚያችም ሌሊት ኢያሱ ወደ ሸለቆው ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እነርሱም ዋናውን ሠራዊት ከከተማ በስተሰሜን በኩል፥ የኋላውን ደጀን በስተምዕራብ በኩል አሰለፉ፤ ኢያሱ ግን ሌሊቱን በሸለቆው አሳለፈ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 8:13
3 Referencias Cruzadas  

አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል ደብቆ አስቀመጣቸው።


የጋይም ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ቸኩለው በማለዳ ተነሡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወጡ፤ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር እንዳለ አያውቅም ነበር።


በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ እንደ ጌታ ቃል አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos