La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በወጡ ጊዜ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም የብስ በረ​ገጡ ጊዜ፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ተወ​ር​ውሮ ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናቱ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ከውሃው በመውጣት እግራቸው ደረቁን መሬት ልክ ሲነካ የዮርዳኖስ ውሃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ እንደ ቀድሞው ሁሉ ሞልቶ በዳሩ ሁሉ ይፈስስ ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜ፥ የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፥ ቀድሞም እንደ ነበረ ከአፉ እስከ ደፉ ሞልቶ በዳርቻው ሁሉ ፈሰሰ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ወጥተው እግሮቻቸው ደረቁን መሬት በረገጡ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ ወደ ቦታው ተመልሶ እንደ ቀድሞው ሞልቶ ይፈስ ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜ፥ የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፥ ቀድሞም እንደ ነበረ በዳሩ ሁሉ ላይ ሄደ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 4:18
8 Referencias Cruzadas  

በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ዮር​ዳ​ኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነ​በረ ጊዜ የተ​ሻ​ገ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ በም​ሥ​ራ​ቅና በም​ዕ​ራብ በኩል የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሁሉ አባ​ረሩ።


ከይ​ሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠ​ፋል፤ ኀያ​ላ​ኑ​ንም ይጨ​ር​ሳል፤ ሰፈ​ሩም በሰ​ፊው ምድ​ርና በሀ​ገ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ይሞ​ላል፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”


እንደ ክረ​ም​ትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮር​ዳ​ኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበ​ርና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦ​ቱን የተ​ሸ​ከ​ሙት የካ​ህ​ናቱ እግ​ሮች በው​ኃዉ ዳር ሲጠ​ልቁ፥


ሕዝ​ቡም ሁሉ አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ ተሻ​ገ​ረች፤ እነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች በፊ​ታ​ቸው ተሻ​ገሩ።


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውጡ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።