Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ዮር​ዳ​ኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነ​በረ ጊዜ የተ​ሻ​ገ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ በም​ሥ​ራ​ቅና በም​ዕ​ራብ በኩል የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሁሉ አባ​ረሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ፣ ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነበረ ጊዜ የተሻገሩት እነዚህ ናቸው፤ በሸለቆውም ውስጥ በምሥራቅና በምዕራብ በኩል የተቀመጡትን ሁሉ አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እነዚህም የጋድ ነገድ አባሎች በአንድ ወቅት የዓመቱ የመጀመሪያ ወር እንደ ገባ፥ የዮርዳኖስም ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ ወንዙን ተሻገሩ፤ ከወንዙ በሰተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ በሸለቆዎቹ ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነበረ ጊዜ የተሻገሩት እነዚህ ናቸው፤ በሸለቆውም ውስጥ በምሥራቅና በምዕራብ በኩል የተቀመጡትን ሁሉ አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 12:15
5 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ወደ ነበ​ረ​ባት ወደ አን​ባ​ዪቱ ከብ​ን​ያ​ምና ከይ​ሁዳ ወገን ሰዎች ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት መጡ።


እግ​ሮ​ችህ ሮጠው ይደ​ክ​ማሉ፤ ፈረ​ሶ​ችን ለምን ታስ​ጌ​ጣ​ለህ? በሰ​ላ​ምም ምድር ላይ ለምን ትታ​መ​ና​ለህ? በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስስ ጩኸት ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?


እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አን​በሳ ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ች​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቃ​ወም እረኛ ማን ነው?”


እንደ ክረ​ም​ትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮር​ዳ​ኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበ​ርና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦ​ቱን የተ​ሸ​ከ​ሙት የካ​ህ​ናቱ እግ​ሮች በው​ኃዉ ዳር ሲጠ​ልቁ፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በወጡ ጊዜ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም የብስ በረ​ገጡ ጊዜ፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ተወ​ር​ውሮ ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos