ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ቂጣ እንጎቻ አድርገው ጋገሩት። አልቦካም ነበርና፤ ግብፃውያንም ስለ አስወጡአቸው ይቈዩ ዘንድ አልተቻላቸውምና፤ ለመንገድም ስንቅ አላሰናዱም ነበርና።
ኢያሱ 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲነግር፥ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ እስኪፈጽም ድረስ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ለኢያሱ በሰጠው መመሪያ መሠረት፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲነግር ኢያሱን ያዘዘው እስኪፈጸም ድረስ፣ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ቈዩ፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ፥ ጌታ ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነግር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበርና፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሕዝቡ እንዲነግር እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ሁሉ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ካህናቱ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል እንደ ቆሙ ቈዩ፤ ሙሴም ኢያሱን ያዘዘው ይህንኑ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥኖ ወንዙን ተሻገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ፥ እግዚአብሔር ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነግር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበርና፥ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። |
ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ቂጣ እንጎቻ አድርገው ጋገሩት። አልቦካም ነበርና፤ ግብፃውያንም ስለ አስወጡአቸው ይቈዩ ዘንድ አልተቻላቸውምና፤ ለመንገድም ስንቅ አላሰናዱም ነበርና።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆነውን፥ የተመረጠውን፥ የከበረውንና መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
ሙሴም ይህችን ሕግ ጻፈ፤ የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት ይሸከሙ ለነበሩት ለሌዊ ልጆች ለካህናቱ፥ ለእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ሰጣት።
ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፤ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞሬዎናዊው፥ ፌርዜዎናዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጤዎናዊው፥ ጌርጌሴዎናዊው፥ ኤዌዎናዊው፥ ኢያቡሴዎናዊው ተዋጉአችሁ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።
እንዲህም ይሆናል፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮርዳኖስ ውኃ ይደርቃል፤ ከላይ የሚወርደውም ውኃ ይቆማል።”
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።