La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 24:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው፣ ከገዓስ ተራራ በስተሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምናሴራ ቀበሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በተራራማው በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ግዛት በተምና-ሴራ ቀበሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያንም ከጋዓሽ ተራራ በስተሰሜን በኩል በምትገኘው በኮረብታማይቱ በኤፍሬም አገር የራሱ የኢያሱ ርስት በሆነችው በቲምናትሴራሕ ቀበሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በተራራማው በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ዳርቻ በተምናሴራ ቀበሩት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 24:30
6 Referencias Cruzadas  

ኤፍ​ራ​ታ​ዊው በና​ያስ፥ የአ​ብ​ሪስ ሰው አሶም፥


በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።


ከዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም አገር አለፉ እስከ ሚካም ቤት ደረሱ።


በተ​ራ​ራ​ማዉ በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት።