አሁንም የእግዚአብሔር ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር ትወርሱ ዘንድ፥ ለልጆቻችሁም ለዘለዓለም ታወርሱአት ዘንድ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ ፈልጉም።
ኢያሱ 24:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ትታችሁ ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ መልካምን ባደረገላችሁ ፋንታ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፤ ያጠፋችሁማል” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ትታችሁ ባዕዳን አማልክትን የምታመልኩ ከሆነ፣ መልካም ነገር ካደረገላችሁ በኋላ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፤ ያጠፋችኋልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ ያጠፋችኋልም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱን ትታችሁ ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩ፥ ደግ ያደረገላችሁ ቢሆንም እንኳ ተመልሶ እርሱ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፤ ያጠፋችሁማል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ ያጠፋችሁማል አላቸው። |
አሁንም የእግዚአብሔር ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር ትወርሱ ዘንድ፥ ለልጆቻችሁም ለዘለዓለም ታወርሱአት ዘንድ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ ፈልጉም።
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
እርሱም ንጉሡን አሳን፥ የይሁዳንና የብንያምን ሕዝብ ሁሉ ሊገናኝ ወጣ፤ እንዲህም አለ፥ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ብትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።
ንጉሡንም፥ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኀይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና፤ በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና።
አቤቱ! የእስራኤል ተስፋ ሆይ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኀጢአትንም ቢሠራ፥ ኀጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ በአደረገው ዐመፅና በሠራት ኀጢአት በዚያች ይሞታል።
እግዚአብሔርም ተለያቸው፤ የሰማይ ጭፍራን ያመልኩም ዘንድ ተዋቸው፤ የነቢያት መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ፤ ‘እናንት የእስራኤል ወገኖች ሆይ፥ በውኑ በምድረ በዳ ሳላችሁ አርባ ዐመት ያቀረባችሁልኝ ቍርባንና መሥዋዕት አለን?
“ልጆችን፥ የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ረዥም ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በበደላችሁም ጊዜ፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል ባደረጋችሁ ጊዜ፥ ታስቈጡትም ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ፥
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አትቀመጡባትም።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትመጣለች።