በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል አንዲቱ ከተማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ትሆናለች፤ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔርዐምድ ይሆናል።
ኢያሱ 22:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም መሠዊያ እንሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለቍርባን አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኛም ‘እንነሣና መሠዊያ እንሥራ፤ የምንሠራው መሠዊያ ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ማቅረቢያ አይውልም’ ያልነው ለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፦ ‘ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ያልሆነን መሠዊያ እንስራ አልን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኛ የሠራነው መሠዊያ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት ለማቅረብ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም፦ መሠዊያ እንስራ አልን፥ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፥ |
በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል አንዲቱ ከተማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ትሆናለች፤ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔርዐምድ ይሆናል።
እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም ይሉአቸዋል፤ በዚሁም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከማምለክ እንዳያወጡአቸው ብለን ይህን አደረግን።
ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል፥ ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቍርባን፥ በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።
በድንኳኑ ፊት ካለው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሰላም መሥዋዕት፥ ለደኅንነት መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”
ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእግዚአብሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤዝሪ አባት በሆነችው በኤፍራታ አለ።