ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
ኢያሱ 22:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይልቁንም ከልባችን ፍርሀት የተነሣ፦ ነገ ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ከእስራኤል ልጆች አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ? እንዳይሉአቸው ስለፈራን ይህን የሠራነው ካልሆነ፥ እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኛማ ይህን ያደረግነው፣ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ለዘሮቻችን እንዲህ እንዳይሏቸው ፈርተን ነው፤ ‘ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ ምን ግንኙነት አላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንም ይህን ያደረግነው ከልባችን ፍርሃት የተነሣ ሲሆን እንዲህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ‘ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ጋር ምን ነገር አላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ የሠራነው ለዚህ አይደለም፤ እኛ እርሱን የሠራነው በሚመጡት ዘመናት የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘እናንተ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን ግንኙነት አላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ? |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደፊት ጻድቅነቴን ይመሰክርልኛል፤ ከፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ የሌለበት፥ ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቈጠርብኝ።”
እንዲህም ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምንድን ነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን፤
አምላካችንን እግዚአብሔርን እንድንክደው፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህልን ቍርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይመራመረን፤
እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም ይሉአቸዋል፤ በዚሁም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከማምለክ እንዳያወጡአቸው ብለን ይህን አደረግን።
እነዚህም ምልክት ይሆኑላችኋል፤ ልጅህ ነገ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ ልጅህን እንዲህ ትለዋለህ፦