Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ይልቁንም ይህን ያደረግነው ከልባችን ፍርሃት የተነሣ ሲሆን እንዲህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ‘ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ጋር ምን ነገር አላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እኛማ ይህን ያደረግነው፣ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ለዘሮቻችን እንዲህ እንዳይሏቸው ፈርተን ነው፤ ‘ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ ምን ግንኙነት አላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እኛ የሠራነው ለዚህ አይደለም፤ እኛ እርሱን የሠራነው በሚመጡት ዘመናት የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘እናንተ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን ግንኙነት አላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ይል​ቁ​ንም ከል​ባ​ችን ፍር​ሀት የተ​ነሣ፦ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ምን አላ​ችሁ? እን​ዳ​ይ​ሉ​አ​ቸው ስለ​ፈ​ራን ይህን የሠ​ራ​ነው ካል​ሆነ፥ እና​ንተ የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 22:24
7 Referencias Cruzadas  

ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።


ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደ ፊት ጻድቅነቴ ይመሰክርልኛል፥ ከፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ የሌለበት ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቆጠርብኝ።”


እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤


“በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፥ ‘አምላካችን ጌታ ያዘዛችሁ ምስክርነቶች፥ ሥርዓት፥ ፍርድስ ምንድነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥


ጌታን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የአንድነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደሆነ ጌታ እርሱ ራሱ ይበቀለን፤


እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ጌታ በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም ይሉአቸዋል።’ በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን ጌታን እንዳይፈሩ ያደርጓቸዋል።


ይህም በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል፤ ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ ‘ለእናንተ እነዚህ ድንጋዮች የሚሰጡት ትርጒም ምንድነው?’ ብለው ሲጠይቁአችሁ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos