የአባቶቻቸውንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው ባዕድ አምላክንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚያም ወራት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ።
ኢያሱ 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኀጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቍጣ አልወረደምን? እርሱም ብቻውን ቢበድል በኀጢአቱ ብቻውን ሞተን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዛራ ልጅ አካን፣ ዕርም የሆነውን ነገር በመውሰድ ኀጢአት ስለ ሠራ፣ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ላይ ቍጣ አልመጣምን? በሠራው ኀጢአት የሞተውም እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ስላልታመነ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በበደሉ ብቻውን አልሞተም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዛራ ልጅ ዓካን መደምሰስ በሚገባቸው ነገሮች እምነተቢስ ሆኖ ትእዛዝ በማፍረሱ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደምን? በጥፋቱም የጠፋው እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአቱ ብቻውን አልሞተም። |
የአባቶቻቸውንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው ባዕድ አምላክንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚያም ወራት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ።
ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን፥ “እንዳትሞቱ፥ በማኅበሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እንዳይወርድ ራሳችሁን አትንጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ እግዚአብሔር ስላቃጠላቸው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።
በዘንበሪም ወገን ምልክት ታየ፤ የዘንበሪም ቤተ ሰብ እያንዳንዱ ተለየ፤ ከይሁዳም ወገን በሆነ በከርሚ ልጅ በዘንበሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአካን ላይ ምልክት ታየ።
ኢያሱም የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ልብሱንም፥ ልሳነ ወርቁንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰዳቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ንብረቱንም ሁሉ ወደ ዔሜቃኮር ወሰደ።
የጋይ ሰዎችም ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀምረው እስከ አጠፉአቸው ድረስ አባረሩአቸው፤ በቍልቍለቱም ገደሉአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ደነገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።