ኢያሱ 21:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማርያቸው ጋር ዐሥር ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነመሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸው ጋር ዐሥር ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ የቀሩት የቀዓት ጐሣ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በድምሩ ዐሥር ከተሞች ተረከቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰምርያቸው ጋር አሥር ናቸው። |
ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማርያዋን፥ ቦሶርንና መሰማርያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።