ኢያሱ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “እንደ ቃላችሁ ይሁን” አለች፤ አሰናበተቻቸውም፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “ይሁን፤ ባላችሁት ተስማምቻለሁ” ስትል መለሰች። ከዚያም ሰደደቻቸው፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀይ ፈትሉንም በመስኮቷ ላይ አንጠለጠለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም እንዲህ አለች፦ “እንደ ቃላችሁ ይሁን፤” ከዚያም በኋላ በደኅና አሰናበተቻቸው እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም በዚህ ተስማምታ ሸኘቻቸው፤ እነርሱም ከሄዱ በኋላ ቀዩን ገመድ በመስኮቱ ላይ አንጠለጠለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ እንደ ቃላችሁ ይሁን አለች፥ ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፥ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው። |
እነሆ፥ እኛ ወደ ሀገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው፤ አባትሽንም፥ እናትሽንም፥ ወንድሞችሽንም፥ የአባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብስቢ።
እነርሱም ወጥተው ወደ ተራራው ሄዱ፤ የሚከተሉአቸውና የሚፈልጉአቸውም እስኪመለሱ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፤ በመንገዱም አላገኙአቸውም።