ኢያሱ 19:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴጌነት ይዞራል፤ በመስዕም በኩል ከዛብሎንና ከጋይ ከይፍታሕኤል ይያያዛል ወደ ሳፍቱ ቤታሜሕና ወደ ኢንሂል ይደርሳል፤ ወደ ኮባ ማሾሜልም ያልፋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ቤትዳጎን ይመለስና ዛብሎንንና የይፍታሕኤልን ሸለቆ ይዞ፣ ካቡልን በስተግራ በመተው በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤል ያቀናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት-ዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን ወደ ካቡል ወጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ምሥራቅም ይታጠፍና ድንበሩ ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ነዒኤል በሚወስደው መንገድ ከዛብሎንና ከይፍታሕኤል ሸለቆ እየተዋሰነ ወደ ቤትዳጎን ይዘልቃል። በሰሜንም ወደ ካቡል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፥ በስተ ግራ በኩልም ወደ ካቡል ወጣ፥ |