በጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ አፍ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሔማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።
ኢያሱ 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ጌቤሮ ምሥራቅ ወደ ከታሤም ከተማ ያልፋል፤ ወደ ሪናሞን ወደ ማታርዮዛ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ምሥራቅ በመቀጠል፣ ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሪሞን በመሄድ ወደ ኒዓ ይታጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋት-ሔፍርና ወደ ዒታ-ቃጺን አለፈ፤ ወደ ሪምን በመውጣት ወደ ኒዓ ታጠፈ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም በዚሁ በምሥራቅ በኩል ወደ ሪሞን በሚወስደው መንገድ ወደ ኔዓ አቅጣጫ ይታጠፍና ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፥ ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ። |
በጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ አፍ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሔማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።