La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የድ​ን​በ​ራ​ቸ​ውም ፍጻሜ በሰ​ሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደ​ር​ሳል፤ በደ​ቡ​ብም በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ዮር​ዳ​ኖስ ነው። ይህም በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በር ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሰሜናዊውን የቤትሖግላንን ተረተር ዐልፎ ይሄድና በስተ ደቡብ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚገባበት እስከ ጨው ባሕር ወሽመጥ ይዘልቃል፤ ይህም ደቡባዊ ድንበሩ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፤ የድንበሩም መጨረሻ በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፤ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ድንበሩ በቤትሆግላ ጐን ያልፋል፤ ከጨው ባሕር በስተሰሜን እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ደቡብ ድረስ ይሄዳል። ይህም የደቡቡ ድንበር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፥ መውጫውም በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፥ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 18:19
10 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።


እነ​ዚ​ያ​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ፥ በከ​ተ​ሞ​ችም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ቡቃያ ሁሉ ገለ​በጠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ባሕር ያደ​ር​ቃል፤ በኀ​ይ​ለ​ኛም ነፋስ እጁን በወ​ንዙ ላይ ያነ​ሣል፤ ሰባት ፈሳ​ሾ​ች​ንም ይመ​ታል፤ ሰዎ​ችም በጫ​ማ​ቸው እን​ዲ​ሻ​ገሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


የአ​ዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ዶ​ም​ያስ መያ​ያዣ ይሆ​ናል፤ የአ​ዜ​ብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በም​ሥ​ራቅ በኩል ይጀ​ም​ራል፤


ከመ​ካ​ናራ ወሰን ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥ​ራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እር​ሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረ​ባን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው።


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለ​ውን ዓረባ እስከ ኬኔ​ሬት ባሕር ድረስ፥ በአ​ሴ​ሞት መን​ገድ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ከፋ​ስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለ​ውን ምድር የገ​ዛው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ሴዎን፤


በደ​ቡ​ብም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስ​ከ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ነበረ።


በሰ​ሜ​ንም በኩል ወደ ቤተ ራባ ጀርባ ያል​ፋል። በመ​ስ​ዕም ወደ ባሕር መን​ገድ ይወ​ር​ዳል፤


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ድን​በሩ ዮር​ዳ​ኖስ ነበረ። ይህ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ዳርቻ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የብ​ን​ያም ልጆች ርስት ነበረ።


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።