La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 15:9
8 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ከይ​ሁዳ አለ​ቆች ጋር ተነ​ሥ​ተው በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።


ዳዊ​ትም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መ​ጠ​ውን፥ ስሙም በእ​ር​ስዋ የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከዚያ ያወጡ ዘንድ በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሄዱ።


ባላ፥ ባቆ​ብና አሶም፤


ቴቆ፥ ኤፍ​ራታ፥ ይኽ​ች​ውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎ​ርም፥ ኤጣ​ንም፥ ቁሎን፥ ጠጦ​ንም፥ ሶብ​ሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነ​ኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ቅር​ያ​ት​በ​ኣል፥ ይኽ​ች​ውም የኢ​ያ​ርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


የደ​ቡ​ብም ዳርቻ ከቅ​ር​ያ​ታ​ርም መጨ​ረሻ ነበረ፤ ድን​በ​ሩም በጋ​ሲን ላይ ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።


ወጥ​ተ​ውም በይ​ሁዳ ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነ​ሆም፥ ቦታዉ ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም በስ​ተ​ኋላ ነው።


በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምም ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት መል​ሰ​ዋል፤ ወር​ዳ​ች​ሁም ወደ እና​ንተ ውሰ​ዱ​አት” አሉ።