La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በባ​ሕር በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸ​ውም እስከ ታላቁ ባሕ​ርና እስከ ዳር​ቻው ድረስ ነበረ። ለይ​ሁዳ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በዙ​ሪ​ያው ያለ ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የምድሪቱ ምዕራባዊ ወሰን የታላቁ ባሕር ጠረፍ ነው። እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለውን የይሁዳን ሕዝብ በዙሪያው የከበቡት ወሰኖቹ እነዚሁ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የምዕራባዊው ዳርቻ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና ጠረፉ ድረስ ነው፤ ይህም የይሁዳ ልጆች እንደየወገናቸው ዙሪያ ድንበራቸው ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 15:12
7 Referencias Cruzadas  

የም​ዕ​ራ​ቡም ድን​በር ከደ​ቡቡ ድን​በር ጀምሮ እስከ ሐማት መግ​ቢያ አን​ጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የም​ዕ​ራቡ ድን​በር ይህ ነው።


ከሮ​ቤ​ልም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለይ​ሁዳ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።


ድን​በ​ሩም ወደ አቃ​ሮን ደቡብ ይወ​ጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመ​ለ​ሳል፤ ድን​በሩ ወደ ሰቆት ይወ​ጣል፤ ወደ ደቡ​ብም ያል​ፋል፤ በሌ​ብና በኩ​ልም ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።


አሴ​ያ​ዶት መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም፥ ጋዛም መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕ​ርም ወሰኑ ነው።


በሰ​ባ​ትም ክፍል ይከ​ፍ​ሉ​ታል፤ ይሁዳ በደ​ቡብ በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣል፤ የዮ​ሴ​ፍም ልጆች በሰ​ሜን በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣሉ።