ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰረገላዎችን፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችን፥ ሃያ ሺህም እግረኞችን ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራሱም መቶ ሰረገላዎችን ብቻ አስቀረ።
ኢያሱ 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ እኔ ሁሉንም እንደሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራ፤ ስለ እስራኤል በመዋጋት ነገ ይህን ጊዜ ሁሉንም እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አንተም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፥ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ አለው። |
ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰረገላዎችን፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችን፥ ሃያ ሺህም እግረኞችን ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራሱም መቶ ሰረገላዎችን ብቻ አስቀረ።
ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በአሲስ ዐቀበት ይወጣሉ፤ በሸለቆውም መጨረሻ በኢያርሔል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገኙአቸዋላችሁ።
ነገር ግን፥ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፤ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
ርዳታ ለመፈለግ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፥ በፈረሶችና በሰረገሎችም ለሚታመኑ ወዮላቸው! ፈረሰኞቹ ብዙዎች ናቸውና፤ በእስራኤልም ቅዱስ አልታመኑምና፤ እግዚአብሔርንም አልፈለጉምና።
በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፤ የጦር መሣሪያዎችንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ አላባሽ አግሬ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ የእጅ በትሮችንና ጦርንም ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።
ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን።
እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፣ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።
አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው በፊትህ የሚተርፍ የለም፤” አለው።
ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።
በዚያም ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በፊቷ ይቆም ነበርና። “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንውጣን? ወይስ እንቅር?” አሉ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጡ” አላቸው።
የመጡትንም መልእክተኞች፥ “የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኰሰ ጊዜ ድኅነት ይሆንላችኋል በሉአቸው” አሉአቸው። መልእክተኞችም ወደ ከተማዪቱ መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላቸው።