Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የመ​ጡ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተ​ኰሰ ጊዜ ድኅ​ነት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል በሉ​አ​ቸው” አሉ​አ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፣ “ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፣ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ በደስታ ፈነደቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከያቤሽ የመጡትንም መልእክተኞች “ነገ ከቀትር በፊት የምናድናቸው መሆኑን ለሕዝባችሁ ንገሩ” አሉአቸው። መልእክቱንም ለያቤሽ ሰዎች በነገሩ ጊዜ የያቤሽ ሰዎች እጅግ ተደሰቱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የመጡትንም መልክተኞች፦ የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኮሰ ጊዜ ማዳን ይሆንላችኋል በሉአቸው አሉአቸው። መልክተኞችም መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፥ ደስም አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 11:9
7 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ። እነ​ሆም፥ ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባ​ኤው ማንም አል​ወ​ጣም ነበር።


በባማ ባለው በቤ​ዜ​ቅም ቈጠ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።


የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች፦ ለአ​ሞ​ና​ዊው ናዖስ “ነገ እን​ወ​ጣ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁ​ንም አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በሳ​ኦል ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሰዎች በሰሙ ጊዜ፥ ጀግ​ኖች ሰዎች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ሌሊ​ቱን ሁሉ ሄዱ፥


ዳዊ​ትም ወደ ኢያ​ቢስ ገለ​ዓድ ገዦች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ዳዊ​ትም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቀ​ባው ለጌ​ታ​ችሁ ለሳ​ኦል ይህን ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ እር​ሱ​ንና ልጁን ዮና​ታ​ን​ንም ቀብ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ።


ጽኑ​ዓን ሰዎች ሁሉ ከገ​ለ​ዐድ ተነ​ሥ​ተው የሳ​ኦ​ልን ሬሳ የል​ጆ​ቹ​ንም ሬሳ​ዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ካለው ከት​ልቁ ዛፍ በታች አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios