La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሰዎች ሁሉ በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሳያ​ስ​ቀሩ ሁሉ​ንም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ አሶ​ር​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እስትንፋስ ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤ ራሷን አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፤ አሦርንም በእሳት አቃጠላት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን በሐጾር የተገኘውን ሰው ሁሉ ስለ ገደሉ በሕይወት የተረፈ አልነበረም፤ ከተማይቱም በእሳት ተቃጠለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፥ አሶርንም በእሳት አቃጠላት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 11:11
6 Referencias Cruzadas  

ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።


ከብ​ቶ​ቹን ሁሉ የከ​ተ​ሞ​ቹ​ንም ምርኮ ለእኛ ወሰ​ድን።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በመ​ታ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤


እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ፥ ከወ​ንድ እስከ ሴት፥ ከሕ​ፃን እስከ ሽማ​ግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።


ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ ነገር ግን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የና​ሱ​ንና የብ​ረ​ቱ​ንም ዕቃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።