ኢያሱ 10:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ሁሉ፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በአዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም ፤ እርስዋንም፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዙአትም፤ እርሷንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በዔግሎም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፤ እርሷንም በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋንም ይዘው ንጉሡን፥ በከተማይቱና በአካባቢዋም የገጠር ከተሞች ያገኙትን ሁሉ ገደሉ፤ ኢያሱም ልክ በዔግሎን ባደረገው ዐይነት ከተማይቱ እንድትደመሰስ ፈረደባት፤ በእርስዋም ውስጥ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፥ በኦዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። |
በዚያም ቀን መቄዳን ያዟት፤ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀሩም፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረጉ በመቄዳ ንጉሥ አደረጉ።
እግዚአብሔርም በእስርኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፤ በዚያም ቀን ያዙአት፤ በሰይፍም ስለት መቱአት፤ በላኪስም እንዳደረገው ሁሉ፥ በእርስዋ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ያዙ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፤ በእነርሱም ውስጥ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉ፤ ማንንም አላስቀረም፤ በኬብሮንና በንጉሥዋም እንዳደረገው እንዲሁ በዳቤርና በንጉሥዋ አደረገ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው።