La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 10:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላኪ​ስን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያዙ​አት፤ በል​ብ​ናም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ፥ እር​ስ​ዋን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ለኪሶን አሳልፎ ለእስራኤል ሰጠ፤ ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት፤ በልብና እንዳደረገው ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፥ በሁለተኛውም ቀን ያዙአት፤ በልብናም እንዳደረጉት ሁሉ፥ እርሷን በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱአቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ጦርነቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ለእስራኤላውያን በላኪሽ ላይ ድልን ሰጣቸው፤ በሊብና ባደረጉትም ዐይነት በከተማይቱ ያገኙትን ሰው ሁሉ በሰይፍ ፈጁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፥ በሁለተኛውም ቀን ያዙአት፥ በልብናም እንዳደረጉት ሁሉ፥ እርስዋን በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱአቸው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 10:32
7 Referencias Cruzadas  

ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በል​ብና ሲዋጋ አገ​ኘው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በመ​ታ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤


በዚ​ያም ቀን መቄ​ዳን ያዟት፤ እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ሩም፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረጉ በመ​ቄዳ ንጉሥ አደ​ረጉ።


ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከል​ብና ወደ ላኪስ አለፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ሰፈሩ፤ ከበ​ቡ​አ​ትም።


በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ኢያሱ የእ​ነ​ዚ​ህን መን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያዘ፤ በሰ​ይ​ፍም መታ​ቸው፤ ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው።