La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 10:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፀሐ​ይም ልት​ገባ በቀ​ረ​በች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፤ ከዛ​ፎ​ችም አወ​ረ​ዱ​አ​ቸው፤ ተሸ​ሽ​ገ​ውም በነ​በ​ሩ​በት ዋሻ ጣሉ​አ​ቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዋ​ሻው አፍ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ ተደ​ር​ጎ​አል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፀሓይ ለመጥለቅ በማዘቅዘቅ ላይ ሳለች ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፤ ከዚያም የነገሥታቱን ሬሳ ከዛፎቹ ላይ አውርደው ቀድሞ ተደብቀው ወደ ነበሩበት ዋሻ ውስጥ ጣሏቸው። በዋሻውም አፍ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ፤ ድንጋዮቹም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፀሐይም ልትገባ በቀረበች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ከዛፎችም አወረዱአቸው፥ ተሸሽገውም በነበሩበት ዋሻ ጣሉአቸው፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ ተደርጎአል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፀሐይም ስትጠልቅ የነዚያ ነገሥታት ሬሳ ከየተሰቀለበት እንጨት እንዲወርድና ቀድሞ ተደብቀው ወደነበሩበት ዋሻ ውስጥ እንዲጣል ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፤ ታላላቅ ድንጋዮችንም አንከባለው የዋሻውን ደጃፍ ገጠሙት፤ እስከ አሁን በዚያ ይገኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፀሐይም ልትገባ በቀረበች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ከዛፎችም አወረዱአቸው፥ ተሸሽገውም በነበሩበት ዋሻ ጣሉአቸው፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ ተደርጎአል።

Ver Capítulo



ኢያሱ 10:27
5 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወስዶ በበ​ረሓ ባለ በታ​ላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ረ​በት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሸሽ​ተው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ገቡ።


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።


የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።