ኢያሱ 10:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ “የዋሻውን አፍ ክፈቱ፤ እነዚያንም አምስት ነገሥት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም፤ “ዋሻውን ከፍታችሁ እነዚያን ዐምስቱን ነገሥታት አውጥታችሁ አምጡልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢያሱ፦ “የዋሻውን በር ከፍታችሁ በማውጣት እነዚያን አምስት ነገሥታት ወደ እኔ አምጡ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም፦ የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው አለ። |
ሕዝቡ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ በደኅና ተመለሱ፤ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ማንም ሰው የለም።
እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንንም ንጉሥ፥ የየርሙትንም ንጉሥ፥ የላኪስንም ንጉሥ፥ የአዶላምንም ንጉሥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።
ሳሙኤልም፥ “የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?” አለ።