La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝቡ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ መቄዳ በደ​ኅና ተመ​ለሱ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ምላ​ሱን ማን​ቀ​ሳ​ቀስ የደ​ፈረ ማንም ሰው የለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሰራዊቱ ሁሉ በደኅና ተመልሶ፣ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ መጣ፤ በእስራኤላውያንም ላይ አንዲት ቃል የተናገረ ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝብ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ በደኅና ተመለሱ፤ በእስራኤል ልጆች ላይ ደፍሮ ቃል የሚነናገር ማንም ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የኢያሱ ሰዎች ሁሉ በሰላም ተመልሰው እርሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ማቄዳ መጡ። ከዚህም የተነሣ በምድሪቱ በእስራኤላውያን ላይ ደፍሮ ቃል የሚናገር እንኳ አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝብ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ በደኅና ተመለሱ፥ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ማንም ሰው የለም።

Ver Capítulo



ኢያሱ 10:21
5 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ታላቅ ልዩ​ነ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ እን​ድ​ታ​ውቁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ውሻ ምላ​ሱን አያ​ን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​ባ​ቸ​ውም።


በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በማን ታላ​ግ​ጣ​ላ​ችሁ? በማ​ንስ ላይ አፋ​ች​ሁን ታላ​ቅ​ቃ​ላ​ችሁ? ምላ​ሳ​ች​ሁ​ንስ በማን ላይ ታስ​ረ​ዝ​ማ​ላ​ችሁ?


እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥


ኢያ​ሱም፥ “የዋ​ሻ​ውን አፍ ክፈቱ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም አም​ስት ነገ​ሥት ከዋ​ሻው ወደ እኔ አው​ጡ​አ​ቸው” አለ።