ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
ዮሐንስ 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጎረቤቶቹና ቀድሞ የሚያውቁት፥ ሲለምንም ያዩት የነበሩት ግን፥ “ይህ በመንገድ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለም?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎረቤቶቹና ከዚህ ቀደም ብሎ ሲለምን ያዩት ሰዎች፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐረቤቶቹና ቀድሞ ሲለምን አይተውት የነበሩ “ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐረቤቶቹና ቀድሞ ሲለምን ያዩት የነበሩ ሰዎች፥ “ይህ ሰው ያ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐረቤቶቹም ቀድሞም ሲለምን አይተውት የነበሩ፦ “ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አይደለምን?” አሉ። |
ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ፦ ይህች ኑኃሚን ናትን? እያሉ ተንጫጩ።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።
የአንኩስ ብላቴኖችም፥ “ይህ ዳዊት የሀገሩ ንጉሥ አይደለምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘፈን የዘመሩለት እርሱ አይደለምን?” አሉት።