ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ዮሐንስ 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም የዚያን ያየውን ሰው ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወለደ፥ እንዳየም አላመኑም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድ ወደ ወላጆቹ ልከው እስኪያስጠሯቸው ድረስ፣ ሰውየው ዐይነ ስውር እንደ ነበረና እንዳየ አላመኑም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድ የዚያን ማየት የቻለውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ፥ ዐይን ሥውር እንደ ነበረና ማየትም እንደ ጀመረ አላመኑም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሰው ዕውር እንደ ነበረና ዐይኖቹም በኋላ እንዴት እንደ ተከፈቱ ወላጆቹን ጠርተው እስከ ጠየቁአቸው ድረስ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች አላመኑም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድ የዚያን ያየውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕውር እንደ ነበረ እንዳየም ስለ እርሱ አላመኑም፥ |
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
አብርሃምም፦ ‘ሙሴንና ነቢያትን ካልሰሙማ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ቢኖርም እንኳ አይሰሙትም፤ አያምኑትምም’ አለው።”
አይሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠይቁት ዘንድ ካህናትንና ሌዋውያንን ከኢየሩሳሌም በላኩ ጊዜ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
ከባልንጀራችሁ ክብርን የምትመርጡ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም ክብርን የማትሹ እናንተ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?
ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ በእርሱ የሚያምን ቢኖር ከምኵራብ ይውጣ” ብለው አይሁድ ተስማምተው ነበርና።