ሣራም አብርሃምን አለችው፥ “ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አባርራት፤ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና።”
ዮሐንስ 8:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባርያ ዘወትር በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለዓለም ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሪያ ለዘለቄታ በቤተ ሰቡ ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ምን ጊዜም በቤት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘለዓለም ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ ሁልጊዜ በቤት ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ሁልጊዜ በቤት ውስጥ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘላለም ይኖራል። |
ሣራም አብርሃምን አለችው፥ “ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አባርራት፤ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና።”
ነገር ግን ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነፃነት ዓመት ድረስ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለአለቃው ይመለስ፤ ርስቱ ግን ለልጆቹ ይሁን።