ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ጌታችን ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱም አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር።
ዮሐንስ 7:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ክርስቶስ ነው” ያሉም አሉ፤ እኩሌቶቹም እንዲህ አሉ፥ “በውኑ ክርስቶስ ከገሊላ ይወጣልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎችም፣ “እርሱ ክርስቶስ ነው” አሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲህ አሉ፤ “ክርስቶስ ከገሊላ እንዴት ሊመጣ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎች “ይህ ክርስቶስ ነው፤” አሉ፤ ሌሎች ግን “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን? አሉ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች “ይህ መሲሕ ነው” አሉ። ሌሎቹ ግን “መሲሕ የሚመጣው ከገሊላ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎች፦ “ይህ ክርስቶስ ነው” አሉ፤ ሌሎች ግን፦ “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን? |
ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ጌታችን ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱም አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር።
ፊልጶስም ናትናኤልን አገኘውና፥ “ሙሴ በኦሪት፥ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው” አለው።
ናትናኤልም፥ “በየት ታውቀኛለህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ በበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይችሃለሁ” አለው።
ሴቲቱንም፥ “እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለም መድኀኒት ክርስቶስ እንደ ሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ በአንቺ ቃል ያመንበት አይደለም” አሏት።
ከሕዝቡም ብዙዎች አመኑበትና፥ “በውኑ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው ተአምራት የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።