እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም።
ዮሐንስ 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትሹኛላችሁ፤ አታገኙኝምም፤ እኔ ወደምሄድበትም እናንተ መምጣት አትችሉም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበት፥ እናንተ መምጣት አትችሉም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም” አለ። |
እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም።
ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤ እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
አባት ሆይ፥ የሰጠኸኝ እነዚህ እኔ ባለሁበት አብረውኝ ይኖሩ ዘንድና የሰጠኸኝን ክብሬን ያዩ ዘንድ እወድዳለሁ፤ ዓለም ሳይፈጠር ወድደኸኛልና።