La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከራሱ የሚ​ና​ገር የራ​ሱን ክብር ይሻል፤ የላ​ከ​ውን ያከ​ብር ዘንድ የሚ​ፈ​ልግ ግን እው​ነ​ተኛ ነው፤ ሐሰ​ትም የለ​በ​ትም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከራሱ የሚናገር፣ ያን የሚያደርገው ለራሱ ክብርን ስለሚሻ ነው፤ ስለ ላከው ክብር የሚሠራ ግን እርሱ እውነተኛ ነው፤ ሐሰትም አይገኝበትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከገዛ እራሱ የሚናገር የገዛ እራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እርሱ እውነተኛ ነው፤ በእርሱም ዐመፃ የለበትም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከገዛ ራሱ የሚናገር የገዛ ራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላኪውን ክብር የሚፈልግ ግን እውነተኛ ነው፤ ሐሰትም የለበትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እርሱ እውነተኛ ነው በእርሱም ዓመፃ የለበትም።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 7:18
19 Referencias Cruzadas  

ሙሴም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሱን ቢያ​ሳ​ድር አንተ ስለ እኔ ትቀ​ና​ለ​ህን?” አለው።


እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ!


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሰምቶ እን​ዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይ​ደ​ለም።”


አባት ሆይ፥ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው።” ከሰ​ማ​ይም፥ “አከ​በ​ር​ሁህ፤ ደግ​ሞም እን​ደ​ገና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤” የሚል ቃል መጣ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና።


እኔ ከሰው ክብ​ርን ልቀ​በል አል​ሻም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ራሴን ባከ​ብር ክብሬ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም፤ የሚ​ያ​ከ​ብ​ረ​ኝስ እና​ንተ አም​ላ​ካ​ችን የም​ት​ሉት አባቴ አለ።


የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም።


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።


ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ።