ዮሐንስ 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታንኳም ወጡ፤ ወደ ባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆምም ሄዱ፤ እነሆም፥ ፈጽሞ ጨለማ ሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጀልባውም ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሡ። ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። ከወዲሁ ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም አመሩ፤ በዚያን ሰዓት ጊዜው ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። አሁንም ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤ |
ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ፥ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ።
ጌታችን ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወደ አደረገበት የገሊላ ክፍል ወደምትሆን ወደ ቃና ዳግመኛ ሄደ። በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት የንጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤