ሲወርድም አገልጋዮቹ ተቀበሉትና፥ “ልጅህስ ድኖአል” ብለው ነገሩት።
በመንገድ ላይ እንዳለም፣ ባሮቹ አግኝተውት ልጁ በሕይወት መኖሩን ነገሩት።
እርሱም ሲወርድ ሳለ አገልጋዮቹ ተገናኙትና “ብላቴናህ በሕይወት አለ፤” ብለው ነገሩት።
ሲሄድም አገልጋዮቹ በመንገድ አገኙትና “ልጅህ ድኖአል” ብለው ነገሩት።
እርሱም ሲወርድ ሳለ ባሮቹ ተገናኙትና፦ ብላቴናህ በሕይወት አለ ብለው ነገሩት።
ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፥ ለእናቱም ሰጣት፥ “እነሆ፥ ተመልከች ልጅሽ ድኖአል” አለ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሂድ፤ ልጅህስ ድኖአል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታችን ኢየሱስ በነገረው ቃል አምኖ ሄደ።
የዳነባትን ሰዓቷንም ጠየቃቸው፤ “ትናንትና በሰባት ሰዓት ንዳዱ ተወው” አሉት።
አባቱም፥ ጌታችን ኢየሱስ፥ “ልጅህ ድኖአል” ባለበት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እርሱም፥ ቤተ ሰቦቹም ሁሉ አመኑ።