ዮሐንስ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ አላጠመቀም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳሩ ግን ያጠመቀው ኢየሱስ ሳይሆን ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳን ደቀመዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ እራሱ ባያጠምቅም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ያጠምቁ የነበሩት የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንጂ እርሱ ራሱ አያጠምቅም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም። |
ወደ ዮሐንስም ሄደው፥ “መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነበረው፥ አንተም የመሰከርህለት እርሱ እነሆ፥ ያጠምቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄዳል” አሉት።
በኢየሱስ ክርስቶስም ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ጥቂት ቀን አብሮአቸው እንዲቀመጥ ጴጥሮስን ማለዱት።