የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ዮሐንስ 3:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምስክርነቱን የተቀበለ ግን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስክርነቱንም የተቀበለ ሰው፣ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አረጋገጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስክርነቱን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደሆነ አረጋገጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል ግን እግዚአብሔር እውነተኛ መሆኑን ያረጋግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። |
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ አለኝ፤ የላከኝም እውነተኛ ነው፤ እኔ በእርሱ ዘንድ የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።”
ሳይገዘር እግዚአብሔር አብርሃምን በእምነት እንደ አጸደቀው በእርሱ ላይ ይታወቅ ዘንድ ግዝረትን የጽድቅ ማኅተም ትሆነው ዘንድ ምልክት አድርጎ ሰጠው። ሳይገዘሩ ለሚያምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብርሃም በእምነት እንደ ከበረ እነርሱም በእምነት እንደሚከብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።
ለሌሎች ሐዋርያቸው ባልሆንም ለእናንተስ ሐዋርያችሁ እኔ ነኝ፤ በጌታችን የሐዋርያነቴ ማኅተም እናንተ ናችሁና።
እናንተም ልትድኑበት የተማራችሁትን የእውነት ቃል ሰምታችሁና አምናችሁ፤ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ።
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።
ስለዚህም እግዚአብሔር ተስፋውን ለሚወርሱ ሰዎች ምክሩን እንደማይለውጥ ሊገልጥ ወደደ፤ እንደማይለውጥም በመሓላ አጸናው።