ዮሐንስ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም የሰው ልጅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። |
ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
ከላይ የመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የተገኘውም ምድራዊ ነው፤ የምድሩንም ይናገራል፤ ከሰማይ የመጣው ግን ከሁሉ በላይ ነው።
“እኛ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?” አሉ።
“ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው ይህ እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንስ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እኔ በገዛ እጄ የመጣሁ አይደለሁም፤ እርሱ ላከኝ እንጂ።
አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ እርስዋን የሚያመጣልን ማንነው? እንዳትል በሰማይ አይደለችም።