ዮሐንስ 21:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “ኑ፥ ምሳ ብሉ” አላቸው፤ ከደቀ መዛሙርቱም አንተ ማነህ? ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ የለም፤ ጌታችን እንደ ሆነ ዐውቀዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም “ኑ፤ ቍርስ ብሉ” አላቸው። ጌታ እንደ ሆነ ዐውቀው ስለ ነበር፣ ከደቀ መዛሙርቱ፣ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ለመጠየቅ የደፈረ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “ኑ፤ ብሉ” አላቸው። ከደቀ መዛሙርቱ አንድ እንኳን “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም፤ ጌታ መሆኑን አውቀው ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “ኑ ብሉ” አላቸው። ጌታ ኢየሱስ መሆኑን ሁሉም ዐውቀው ስለ ነበር፥ ከደቀ መዛሙርቱ አንድ እንኳ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ “ኑ፥ ምሳ ብሉ” አላቸው። ከደቀ መዛሙርቱ አንድ ስንኳ፦ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊመረምረው የደፈረ አልነበረም፤ ጌታ መሆኑን አውቀው ነበርና። |
እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉትም፤ እንዳይመረምሩት ከእነርሱ የተሰወረ ነውና፤ ስለዚህ ነገርም እንዳይጠይቁት ይፈሩት ነበርና።
ጌታችን ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐውቆ እንዲህ አላቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንደገናም ታዩኛላችሁ” ስለ አልኋችሁ፥ ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?
ስምዖን ጴጥሮስም ወደ ታንኳ ገብቶ መቶ አምሳ ሦስት ታላላቅ ዓሣዎችን መልቶ የነበረውን መረብ ወደ ምድር ሳበ፤ ብዛቱም ይህን ያህል ሲሆን መረቡ አልተቀደደም።
ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ፦ ስምዖን ጴጥሮስን፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አለው፤ እርሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “በጎችን ጠብቅ” አለው።
በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነጋገር ነበርና ተደነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻለህ? ወይስ ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ያለው የለም።
ይኸውም ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን አስቀድሞ ለመረጣቸውና ምስክሮች ለሚሆኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመረጣቸው የተባልንም እኛ ነን፤ ከሙታንም ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።